=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
እውነተኛ የእህትነት ፍቅር ከኢስላም የመመሪያ ብርሃን የሚመነጭ ግኑኝነት ወይም ማህበሪዊ ትስስር ሲሆን ይህ ፍቅር በማንኛውም አለማዊ አና ስውር በሆነ ጥቅም ያልተመረዘ ነው። አንዲትን ሙስሊም ሴት ጁኦግሪፊያዊ መነሻ ፣ ጐሳ ፣ የቆዳ ቀለም ፣ የአይን ቀለም ወይም የፀጉር ቴክስቸር እና ቇንቇ ሳይገድባት ከእህቶቿ ጋር ልብ ለ ልብ የሚያስተሳስር ብቸኛ ሰንሰለት ነው። ሰንሰለቱም መሰረት ያደረገው የአሏህን(ሱ.ወ.ተ) እምነት ነው።
=<({አል-ቁርአን 49:10})>=
{10} አማኞች ወንድማማቾች ናቸው። በመካከላቸውም እርቅን ፍጠሩ። እናም ምህረትን ታገኙ ዘንድ አሏህን ፍሩ።
۩ ይህ ፍቅር አንዱ የእምነት ጥፍጥና መገለጫ ነው።
አል-ቡሐሪ ጥራዝ 1 መጽሃፍ 1 የሃዲስ ቁጥር 15
አነስ እንደተረከው
መልእክተኛው(ሰ.ዐ.ወ) የሚከተሉት ሶስት ባህሪያቶች ያሉት ሰው የእምነት ጥፍጥና ይኖረዋል ብለዋል።
1) አሏህ እና መልእክተኛው ከማንኛውም ነገር በላይ ውድ የሆኑለት
2) ሰውን የሚወድና ውዴታውም ለአሏህ ብሎ የሆነ
3) ወደ ጀሃነም እሳት መወርወር እንዲሚጠላ ሁሉ መክፍርን(መጥመምን) የሚጠላ የሆነ
እናም ይህ ፍቅር እውቅናን ፣ ስልጣንን ፣ ዝናን እና ክብርን ለማግኘት ተብሎ ያልሆነ ሲሆን ንፁህ እና ብርሃን የሆነ ቀልብን የሚፈልግ ውዴታ ነው። ከሰው ልብ ጥላቻን ፣ ቅናትን እና ባላንጣነትን ለማጥፈት ብቸኛው መንገድ ለአሏህ ብሎ መዋደድ ነው።
۩ እናም ውድ ሙስሊም እህቶቼ አሏህ በእሱ መንገድ ከተዋደዱት፤ በእሱም መንገድ ተባብረው ከሚሰሩትና አርሽ ጥላ ስር ከሚቀመጡት፤ አብረው ከሚቀሰቀሱትም ያድርጋችሁ። አሏህ ኢማን እና ተቅዋን ያጐናፅፋችሁ። አሚን!!!
* እኔ ለአሏህ ብየ እወዳችኋለሁ!!!
©የወጣቱ ተልእኮ
۩Youth-Mission
የወጣቱ ተልእኮ-> page۩
page:
http://facebook.com/youth.mission29
website:
http://youth-mission.mobie.in
'~'-.,__,.-'~'
_,.-'~''~'-.,_
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|